Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት በሕጉና በሥርዓቱ መሠረት ሥርዓቱን ይፈጽሙ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዓሉንም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በተወሰነው ሕግና ሥርዐት መሠረት ሁሉ አክብሩ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚህ ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ፥ በተወሰነለት ጊዜ ታደርጉታላችሁ፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ደንቡም ሁሉ ታደርጉታላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊ​ዜው አድ​ር​ጉት፤ እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ እንደ ፍር​ዱም ሁሉ አድ​ር​ጉት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚህ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 9:3
10 Referencias Cruzadas  

የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።


ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በግብጽ ምድር እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤


“እግዚአብሔር የሚከበርበት የፋሲካ በዓል የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጀንበር ጠልቃ መሸትሸት ሲል ይጀመራል፤


“እስራኤላውያን የፋሲካውን በዐል በተወሰነለት ጊዜ ያክብሩ፤


ስለዚህ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለሕዝቡ ነገራቸው፤


እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ኃጢአትን ለማስወገድ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ ተገልጦአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos