የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና ይረግማቸው ዘንድ በለዓምን ስለ ገዙባቸው ነው፥ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።
ዘኍል 24:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባላቅም ቍጣ በበለዓም ላይ ነደደ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን፦ ጠላቶቼን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሽሽ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባላቅም ቁጣ በበለዓም ላይ ነደደ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ ይኸው ባረክሃቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅ በቊጣ እጆቹን ጨብጦ በለዓምን እንዲህ አለው፤ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠርቼህ ነበር፤ አንተ ግን ስትመርቃቸው ይኸው ሦስተኛ ጊዜህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በበለዓም ላይ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን አለው፦ ጠላቶችን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ |
የእስራኤልን ልጆች በእንጀራና በውኃ ስላልተቀበሉአቸውና ይረግማቸው ዘንድ በለዓምን ስለ ገዙባቸው ነው፥ ነገር ግን አምላካችን እርግማኑን ወደ በረከት መለሰው።
ስለዚህ፥ አንተ የሰው ልጅ፥ ትንቢት ተናገር፥ እጅህን አጨብጭብ፥ የተገደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደጋግም የሚከብባቸው የተገደለ የታላቅ ሰው ሰይፍ ነው።
እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን።