ዘካርያስ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ ላይ ያለው ቍስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው፦ “ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድነው?” ብሎ ቢጠይቀው፥ እያንዳንዱም፦ “በወዳጆቼ ቤት የቈሰልኩት ቁስል ነው” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ‘ታዲያ ይህ በሰውነትህ ላይ ያሉት ቊስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጄ ቤት የቈሰልኩት ነው’ ብሎ ይመልስለታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል። |
ኢዩም በእጁ ቀስቱን ለጠጠ፤ ኢዮራምንም በጫንቃው መካከል ወጋው ፤ ፍላጻውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረገላውም ውስጥ በጕልበቱ ላይ ወደቀ።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
ጲላጦስም መልሶ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? Aረ ምን አድርገሃል?” አለው።
የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”