ብዛታቸው የማይቈጠር የሞቱ ሰዎች እርስ በርሳቸው በወደቁ ጊዜ በበሽተኞቹና በሕያዋኖቹ መካከል ቁሞ መቅሠፍቱን ጸጥ አደረገ። ለሕያዋንም መንገድን ለየ።
ቁጣን ባቆመውና ወደ ሕያዋንም እንዳይጠጋ ባገደው ጊዜ፥ አስክሬኖች ተከምረው ነበር።