ሮሜ 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ለሮጠና ለቀደመ አይደለም፤ እግዚአብሔር ይቅር ላለው ነው እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ይህ ለፈለገ ወይም ለሮጠ አይደለም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእግዚአብሔር ምርጫ የሚገኘው በሰው ፈቃድና በሰው ሥራ ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። |
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።
በዚያች ሰዓትም ጌታችን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እንዲህም አለ፥ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጥኸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲሁ ሆኖአልና።
ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የሚወለድ ሁሉ እንዲሁ ነው።”
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ በከንቱ እንዳልሮጥ፥ ወይም በከንቱ ሮጬ እንዳልሆነ፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል አለቆች መስለው ለሚታዩት አስታወቅኋቸው።