ሮሜ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ሌላውን የምታስተምር ራስህን እንዴት አታስተምርም? አትስረቁ ትላለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰርቃለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ፣ ትሰርቃለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ እየሰበክ ትሰርቃለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎችን የምታስተምር ስትሆን ታዲያ ራስህን ለምን አታስተምርም? አትስረቁ ትላለህ፤ አንተ ግን ትሰርቃለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን? |
ሁሉም ከቶ የማይጠግቡ የረከሱ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ ክፉዎች ናቸው፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው እንደ ፈቃዳቸው መንገዳቸውን ተከትለዋል።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
እርሱም እንዲህ አለው፤ “ለእናንተ ለሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸክሙታላችሁ፤ እናንተ ግን ያን ሸክም በአንዲት ጣታችሁ እንኳን አትነኩትም።
ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ።
እርሱም፥ “በውኑ ባለ መድኀኒት ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም ያደረግኸውንና የሰማነውን ሁሉ በዚህም በሀገርህ ደግሞ አድርግ ብላችሁ ይህችን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ” አላቸው።
ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር፥ እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ፥ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ።