La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ራእይ 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣ በእሳት ትቃጠላለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።

Ver Capítulo



ራእይ 18:8
18 Referencias Cruzadas  

እርሱ በኀ​ይል ይይ​ዛ​ልና፤ ፍር​ዱን ማን ይቃ​ወ​ማል?


ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ​ንና ጅራ​ትን፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን በአ​ንድ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ይቈ​ር​ጣል።


ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የሚ​ቤ​ዢ​አ​ቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ያሳ​ርፍ ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ያውክ ዘንድ ጠላ​ቶ​ቹን ወቀሳ ይወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”


ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ፤ በበ​ደ​ልዋ አት​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እር​ሱም ብድ​ራ​ቷን ይከ​ፍ​ላ​ታ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ትልቁን ኀይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”


በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ “በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና፤” እያሉ ጮኹ።


ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ።