እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
ራእይ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ በዚያም አንዲት ሴት በስድብ ስሞች በተሞላ፣ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ባሉት ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ በሁለንተናው የስድብ ስሞች በተጻፉት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ባሉት በቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች አንዲት ሴት አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። |
እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር፥ ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር።
እነርሱም፥ “እነሆ፥ ከአገልጋዮችህ ጋር አምሳ ኀ`ያላን ሰዎች አሉ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዮርዳኖስ ወይም ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ኮረብታ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታህን ይፈልጉት” አሉት። ኤልሳዕም፥ “አትላኩ፤” አላቸው።
በልጅ ወንድምዋ ላይ ተደግፋ እንደ ማለዳ ደምቃና አብርታ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ አማጠችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ ወለደችህ።
መንፈስም ወደ ላይ ወሰደኝ፤ በኋላዬም፥ “የእግዚአብሔር ክብር ከቦታው ይባረክ” የሚል የታላቅ ንውጽውጽታ ድምፅ ሰማሁ።
እጅ መሳይንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ ቅንአት የተባለው ምስል ወደ አለበት አመጣኝ፤
ከውኃዉም ከወጡ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባዉም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ እያለውም መንገዱን ሄደ።
“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።
ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤
ጭነትም ወርቅና ብር፥ የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር፥ ቀይም ሐር፥ ሐምራዊም ልብስ፥ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት፥ ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥
“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤
በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤