መዝሙር 90:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣ ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሠኘን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ አሰኘን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመከራ ዓመቶች አሳልፈናል፤ ብዙ ሐዘንም ደርሶብናል፤ በዚህ ሁሉ ልክ ደስታን ስጠን። |
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፤ ዓለምም ደስ ይለዋል፤ እናንተ ግን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።