ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ለሞት ቀርባለችና።
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።
አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! አስደናቂ ነገሮች ስለ አንቺ ተነግረዋል።
ለርስቱ እኛን መረጠን፥ የያዕቆብን ውበት የወደደ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና።”
ከጽዮን ታዳጊ ይመጣል፤ ከያዕቆብም ኀጢአትን ያርቃል።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘለዓለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነዋል ብሎአልና፤
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፤ እርስዋንና አውራጃዎችዋንም በአሕዛብ መካከል አድርጌአለሁ፥
አየሁም፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።