አምላካችንና መድኀኒታችን ሆይ፥ መልሰን፥ ቍጣህንም ከእኛ መልስ።
ብፁዓን ናቸው፤ በቤትህ የሚኖሩ፣ እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ
ወፍ ለእርሷ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፥ በመሠውያህ አጠገብ፥ የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥
ዘወትር የምስጋና መዝሙር ለአንተ እያቀረቡ በመቅደስህ የሚኖሩ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
ይህች ትውልድ እርሱን ትፈልገዋለች፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት ትፈልጋለች።
እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤ ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
በማለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እገለጥልሃለሁም።
ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች።
እርሱ ይኖራል፥ ከዓረብም ወርቅን ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ስለ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይመርቁታል።
ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ይገዛል።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።