ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ድሃና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
ነፍሴ በተማረረች ጊዜ፣ ልቤም በተቀሠፈ ጊዜ፣
ልቤ ነድዶአልና፥ ኩላሊቴም ቀልጦአልና፥
ኅሊናዬን በጣም መረረው፤ ልቤም ተሰበረ።
ተዘልዬ ስኖርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላማም አድርጎ አቆመኝ፤ እንደ ጉበኛም ተመለከተኝ።
አቤቱ፥ በመዓትህ አትቅሠፈኝ፥ በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።
ነፍሴ ስድብን ጠግባለችና፥ ለሥጋዬም ድኅነትን አጣሁ።
ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜ በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ።