መዝሙር 29:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥ የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ ድምፁም ባለ ግርማ ነው። |
እግዚአብሔርም የድምፁን ክብር ያሰማል፤ የክንዱንም መፈራት፥ በጽኑ ቍጣና በምትበላ እሳት፥ በወጀብም፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በበረዶም ድንጋይ ይገልጣል።
የኪሩቤልም የክንፎቻቸው ድምፅ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።
እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ከጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ሁሉም ደነገጡ፤ እርስ በርሳቸውም ተነጋገሩ፤ እንዲህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምንድን ነው? ክፉዎችን አጋንንት በሥልጣንና በኀይል ያዝዛቸዋልና፥ እነርሱም ይወጣሉና።”
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።