La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የል​ጅ​ነ​ቴን ኀጢ​አ​ትና ስን​ፍ​ና​የን አታ​ስ​ብ​ብኝ። አቤቱ፥ ስለ ቸር​ነ​ትህ ብዛት፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ዐስ​በኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንት በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።

Ver Capítulo



መዝሙር 24:7
23 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ ለማ​ገ​ል​ገል ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት።


አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ለምን ተው​ኸኝ? የኀ​ጢ​አቴ ቃል እኔን ከማ​ዳን የራቀ ነው።


ወደ አንተ ጮኹ፥ ዳኑም፥ አን​ተ​ንም አመኑ፥ አላ​ፈ​ሩም።


በነ​ጋ​ሪ​ትና በመ​ለ​ከት ድምፅ፥ በን​ጉሡ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እልል በሉ።


ፍት​ሕን የሚ​ጠ​ብ​ቅና ጽድ​ቅን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮ​ችን ክፈቱ።


ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕ​ዝ​ቤም መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ከጎ​ዳ​ናው አስ​ወ​ግዱ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አላማ ያዙ።


አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።


ወንድሞቼ ሆይ! በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።