መዝሙር 120:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጁ ይጋርድህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሜሼኽ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቄዳር ሕዝብ መካከል በሜሼክ ስደተኛ ሆኜ በመኖሬ ወዮልኝ! |
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።
እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ።
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ዓረብና የቄዳር አለቆች ሁሉ የእጅሽ ነጋዴዎች ነበሩ፤ በግመሎችና በአውራ በጎች፥ በፍየሎችም በእነዚህ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮስ የሞሣሕና የቶቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤
“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።
ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።