ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
መዝሙር 102:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ይቅርታው ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድኾችን ጸሎት ይሰማል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። |
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።
እኔም መልሼ፥ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ንጹሓን ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ዕድል ፋንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም” አልኋቸው።
ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትድግና ይይ፤ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።”
የባርያውን ቃል ያጸናል፤ የመልእክተኞቹንም ምክር ይፈጽማል። ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፤ የይሁዳንም ከተሞች ትታነጻላችሁ፤ ምድረ በዳዎችዋም ይለመልማሉ፤” ይላል፤
“ከአናምሄል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና።
ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በመከራህም ጊዜ በልብህም ሁሉ፥ በነፍስህም ሁሉየፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።