ምሳሌ 8:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያገኘኝ ሁሉ ሕይወትን ያገኛልና፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና። ከጌታም ሞገስን ያገኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን የሚያገኝ፥ ሕይወትን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛል። |
ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታልና።
በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር የቍጣ መቅሠፍት በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
ክርስቶስን አገለግለው ዘንድ፥ ሁሉን የተውሁለት፥ እንደ ጕድፍም ያደረግሁለት የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና ገናናነት ስለማውቅ ሁሉን እንደ ኢምንት ቈጠርሁት።