ኃጥእ በጻድቅ ዘንድ የተናቀ ነው፥ ኃጥእም የጻድቅ ቤዛ ነው።
ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።
ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።
በደጋግ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በክፉ ሰዎች ላይ ይደርሳል፤ በቀጥተኛ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በእምነተ ቢሶች ላይ ይመጣል።
ጻድቅ ከወጥመድ ያመልጣል፥ ኀጢአተኛ ግን በእርሱ ፋንታ ይሰጣል።
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤