እርስዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ለባሪያዉ ለይስሐቅ ያዘጋጃት ሚስት እርስዋ ትሁን። በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ምሳሌ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶች ለልጆቻቸው ቤትንና ሀብትን ያወርሳሉ፤ ሚስት ግን በእግዚአብሔር ከባልዋ ጋር አንድ ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤ አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳሉ፥ አስተዋይ ሚስት ግን ከጌታ ዘንድ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ቤትና ሀብት ከወላጆቹ ሊወርስ ይችላል፤ አስተዋይ ሚስትን የሚሰጥ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው። |
እርስዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ለባሪያዉ ለይስሐቅ ያዘጋጃት ሚስት እርስዋ ትሁን። በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ከአባቴ ቤት፥ ከተወለድሁባት ምድር ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፤ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
እነሆ ወደ እናንተ ልመጣ ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ነገር ግን አልተፋጠንሁም ገንዘባችሁን ያይደለ፥ እናንተን እሻለሁና፤ ልጆች ለወላጆቻቸው ያይደለ ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያከማቹ ይገባልና፤
ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
የሰውዬውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቤግያ ነበረ፤ ሴቲቱም ደግና ብልህ፥ መልክዋም እጅግ የተዋበ ነበረ፤ ሰውዬው ግን ጨካኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብሩም ክፉ ነበረ።