ምሳሌ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ በንጉሥ አፍ አለ፥ አፉም በፍርድ አይሳሳትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ከንፈሮች እንደ አምላክ ቃል ይናገራሉ፤ አንደበቱ ፍትሕን ያዛባ ዘንድ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ብይን በንጉሥ አፍ ነው፥ አፉም በፍርድ አይስትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ የሚፈርደው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ሥልጣን ነው፤ ስለዚህ ውሳኔዎቹ ዘወትር ትክክል ናቸው። |
ንጉሡም የፈረደውን ፍርድ እስራኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍርድን ለማድረግ የእግዚአብሔር ጥበብ በእርሱ ላይ እንደ ነበረ አይተዋልና ከንጉሡ ፊት የተነሣ ፈሩ።
ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
የማይረባውን የሐሰት ቃል ይናገራሉ፤ ቃል ኪዳንም ያደርጋሉ፤ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል ፍርድ ይበቅልባቸዋል።
ፍርድን ወደ ቍጣ፥ የእውነትንም ፍሬ ወደ እሬት ለውጣችኋልና፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?