La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ፊልጵስዩስ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ ችግ​ሩ​ንም፥ ምቾ​ቱ​ንም እች​ላ​ለሁ፤ ራቡ​ንም፥ ጥጋ​ቡ​ንም፥ ማዘ​ኑ​ንም፥ ደስ​ታ​ው​ንም፥ ሁሉን በሁሉ ለም​ጀ​ዋ​ለሁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብ፣ ባገኝም ሆነ ባጣ፣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጥቂትም ማግኘትን አውቃለሁ፤ ብዙም ማግኘትን አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ የመጥገብንና የመራብን ብዙ የማግኘትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ማግኘትንም ሆነ ማጣትን ዐውቃለሁ፤ በማንኛውም ቦታ ሆነ በየትኛውም ጊዜ የመጥገብንና የመራብን፥ የማግኘትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።

Ver Capítulo



ፊልጵስዩስ 4:12
15 Referencias Cruzadas  

ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውም ዘንድ መል​ካ​ሙን መን​ፈ​ስ​ህን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ መና​ህ​ንም ከአ​ፋ​ቸው አል​ከ​ለ​ከ​ል​ህም፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ውኃን ሰጠ​ሃ​ቸው።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ እጅ እን​ዲህ ተና​ገ​ረኝ፤ በዚ​ህም ሕዝብ መን​ገድ እን​ዳ​ል​ሄድ አስ​ጠ​ነ​ቀ​ቀኝ፤


ከተ​መ​ለ​ስሁ በኋላ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ከተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ቴ​ንም ስድብ ተሸ​ክ​ሜ​አ​ለ​ሁና አፈ​ርሁ፥ ተዋ​ረ​ድ​ሁም።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።


በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።


ወይስ ራሴን በሁሉ ያዋ​ረ​ድሁ በደ​ልሁ ይሆን? እና​ንተ ከፍ ከፍ ትሉ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ያለ ዋጋ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤ መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤ እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።