ዘኍል 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለማወቅ ሰው ከሚሠራው ኀጢአት ሁሉ የሠሩት ቢኖር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ወንድም ሆነ ሴት በማናቸውም ረገድ ሌላውን ቢበድልና ከዚህም የተነሣ ለእግዚአብሔር ባይታመን በደለኛ ነው መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች ተናገር፦ ወንድ ወይም ሴት በጌታ ላይ ፈጽሞ እምነት በማጉደል ሰው የሚሠራውን ማናቸውንም ኃጢአት ቢሠሩ፥ የሠራው ያ ሰው በደለኛ ነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ከወንዶችም ሆኑ ከሴቶች ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘት በማንም ሰው ላይ በደል ቢፈጽም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይተላለፍ ዘንድ ሰው የሚሠራውን ኃጢአት ቢሠራ፥ በዚያም ሰው ላይ በደል ቢሆን፥ በሠራው ኃጢአት ይናዘዝ፤ |
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤
በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ ደረሱ፤ እንዲህም ብለው ነገሩአቸው
ኢያሱም አካንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝም” አለው።