ዘኍል 22:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ ብሏል” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወሮታህን በእጅጉ እከፍላለሁ፤ የምትለውንም ሁሉ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የምትነግረኝንም ሁሉ አደርግልሃለሁና፥ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፍ ባለ ክብር አከብርሃለሁ፤ የጠየቅከኝንም ሁሉ አደርግልሃለሁ፤ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።” |
ባላቅም በለዓምን፥ “አንተን ለመጥራት የላክሁብህ አይደለምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን?” አለው።
እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል፤ አሁንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበልጣልና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የመረቅኸው ምሩቅ፥ የረገምኸውም ርጉም እንደ ሆነ አውቃለሁና” ብሎ ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ።
እነሆም፥ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ ይህ ሦስተኛህ ነው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሂድ፤ እኔ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ።”