ሌዋውያኑም ዐሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን ዐሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
ዘኍል 15:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያም ከምታደርጉት ሊጥ የተለየ ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ዱቄት ላይ አንሥታችሁ ይህን ቍርባን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ እንደ ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቡትን ቁርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለጌታ ትሰጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ከአዲስ እህል ከምትጋግሩት ኅብስት እየተነሣ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ መቅረብ አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ የማንሣት ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። |
ሌዋውያኑም ዐሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን ዐሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
ይህም የተለየ ቍርባን ነውና ከእስራኤልልጆች ዘንድ ለዘለዓለም የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የደኅንነት መሥዋዕታቸው የተለየ ቍርባን ይሆናል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ይሆናል።
የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት ሀገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዐት ነው።
መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ።
“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ከእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ እናንተምከእርሱ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ።