La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 7:73 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

Ver Capítulo



ነህምያ 7:73
7 Referencias Cruzadas  

ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።”


በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞ​ችና በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸው መጀ​መ​ሪያ የተ​ቀ​መጡ ካህ​ናት፥ ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበሩ።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።


ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ሳሉ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡት የሀ​ገሩ አለ​ቆች እነ​ዚህ ናችው፤ እስ​ራ​ኤል ግን ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ የሰ​ሎ​ሞ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ር​ስ​ታ​ቸ​ውና በየ​ከ​ተ​ማ​ቸው በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።


የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ።