ነህምያ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠባቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹሞቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች እስከዚያ ጊዜ ገና አልተናገርሁም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለመኳንንቱ ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ገና ምንም የተናገርሁት ነገር ስላልነበረ፣ ወዴት እንደ ሄድሁ ወይም ምን እንዳደረግሁ ሹማምቱ አላወቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለታላላቆች ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራ ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች ስላልተናገርኩ፥ ሹማምንቱ ወዴት እንደ ሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግሁ አላወቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሀገሪቱ ከነበሩትም ባለሥልጣኖች መካከል የት እንደ ነበርኩና ምን እንዳደረግሁ ያወቀ ማንም አልነበረም፤ ከዚህም በቀር ከአይሁድ ጓደኞቼ ይኸውም ከካህናቱ፥ ከመሪዎቹም ሆነ ከባለሥልጣኖቹ ወይም የሥራው ተካፋዮች ከሚሆኑት ሌሎች ሰዎች ለአንዱም እንኳ የነገርኩት ምንም ነገር አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሹማምቱ ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹማምቱም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች ገና አልተናገርሁም ነበር። |
እኔም፥ “እኛ ያለንበትን ጕስቍልና፥ ኢየሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ። አሁንም ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።