La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሌሊትም ወጥቼ በሸለቆው በር በኩል አድርጌ ወደ ዘንዶው የውሃ ጕድጓድና ወደ ቈሻሻ መድፊያው በር ሄድሁ፤ የፈረሱትንም የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና በእሳት የወደሙትን በሮች ተመለከትሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሸለቆ ቅጽር በር ወጥቼ የዘንዶ ምንጭ ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ በማለፍ፥ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው የጒድፍ መጣያ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄድኩ፤ ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ በማልፍበትም ጊዜ የፈራረሱትን የከተማይቱን ቅጽሮችና በእሳት የወደሙትን የቅጽር በሮች ጐበኘሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ።

Ver Capítulo



ነህምያ 2:13
9 Referencias Cruzadas  

ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች ወደ ቅጥሩ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ አመ​ስ​ጋ​ኞ​ቹ​ንም በሁ​ለት ታላ​ላቅ ተርታ አቆ​ም​ኋ​ቸው፤ የአ​ን​ዱም ተርታ ሰዎች ወደ ቀኝ በቅ​ጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣ​ያው በር ሄዱ።


በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሣሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ር​ገው ዘንድ በልቤ ያኖ​ረ​ውን ለማ​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ሁም፤ ተቀ​ም​ጬ​በት ከነ​በ​ረው እን​ስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እን​ስሳ አል​ነ​በ​ረም።


በሌ​ሊ​ትም በፈ​ፋው በኩል ወጥቼ ቅጥ​ሩን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ገባሁ፤ እን​ዲ​ሁም ተመ​ለ​ስሁ።


እኔም፥ “እኛ ያለ​ን​በ​ትን ጕስ​ቍ​ልና፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ፈረ​ሰች፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠሉ ታያ​ላ​ችሁ። አሁ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ መሳ​ለ​ቂያ እን​ዳ​ን​ሆን ኑና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው።


ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉሡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኑር፤ የአ​ባ​ቶች መቃ​ብር ያለ​ባት ከተማ ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና ፊቴ ስለ ምን አያ​ዝን?” አል​ሁት።


“ወደ ቅጥ​ርዋ ወጥ​ታ​ችሁ አፍ​ርሱ፤ ነገር ግን ፈጽ​ማ​ችሁ አታ​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸ​ውና መጠ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አት​ርፉ።