La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሚክያስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሕዝቤን ሥጋ በሉ፥ ቁርበታቸውን ከላያቸው ላይ ገፈፉ፥ አጥንታቸውን ሰበሩ፤ በአፍላል እንዳለ በድስትም ውስጥ እንደሚከተት ሥጋ ቆራርጠዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሕዝቤን ቆዳ ገፋችሁ አጥንታቸውን ቈራርጣችሁ ለአፍላልና ለድስት እንደሚቈራረጥ ሥጋ አደረጋችኋቸው፤ ሥጋቸውንም በላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።

Ver Capítulo



ሚክያስ 3:3
11 Referencias Cruzadas  

ኀጢ​አ​ተኛ በፊቱ የተ​ናቀ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ሩ​ትን የሚ​ያ​ከ​ብር፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ምሎ የማ​ይ​ከዳ።


በቤተ መቅ​ደ​ስህ እጆ​ችን ባነ​ሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮ​ኽ​ሁ​ትን የል​መ​ና​ዬን ቃል ስማ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ለፍ​ርድ ይመ​ጣል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፥ “ወይ​ኔን አቃ​ጥ​ላ​ች​ኋል፤ ከድ​ሃው የበ​ዘ​በ​ዛ​ች​ሁ​ትም በቤ​ታ​ችሁ አለ፤


ሕዝ​ቤ​ንስ ለምን ትገ​ፋ​ላ​ችሁ? የድ​ሃ​ውን ፊትስ ለምን ታሳ​ፍ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ?”


እነ​ር​ሱም፦ በውኑ ቤቶች በድ​ን​ገት የሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለ​ምን? ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን ብለ​ዋል።


ቍራ​ጭ​ዋ​ንም፥ መል​ካ​ሙን ቍራጭ ሁሉ፥ ጭኑ​ንና ወር​ቹን በእ​ር​ስዋ ውስጥ ጨምር፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ት​ንም አጥ​ን​ቶች ሙላ​ባት።


ችግ​ረ​ኛ​ውን በጥ​ዋት የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ድሃ የም​ት​ቀሙ እና​ንተ ሆይ!


ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፥ ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፥ ሳይፈሩም፥ የሚያልፉትን ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።