የኤልሳዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተኋላው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ” አለ።
ሉቃስ 7:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋበዘውም ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፣ የነካችው ሴት ማን እንደ ሆነች፣ ደግሞም ምን ዐይነት ሰው እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና” ብሎ በልቡ ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና፤” ሲል በልቡ አሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሳ የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነችና ምን ዐይነት ኃጢአተኛ እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤” ሲል በልቡ አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። |
የኤልሳዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተኋላው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ” አለ።
ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።
“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ።
እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።”
እነሆ፥ ከዚያች ከተማ ሰዎችም አንዲት ኀጢአተኛ ሴት በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደተቀመጠ ዐውቃ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ገዝታ መጣች።
በስተኋላውም በእግሮቹ አጠገብ ቆማ አለቀሰች፤ እግሮቹንም በእንባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕርዋም እግሮቹን ታብሰውና ትስመው፥ ሽቱም ትቀባው ነበር።
ዕውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፥ “ሂድ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ፤ ይህ ሰው ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን” አሉት።