La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኮ! ምን ልታዩ ወጣችሁ? ያማረ ልብስ የለበሰውን ሰው ነውን? ባማረ ልብስ የሚሽሞነሞኑና በድሎት የሚኖሩ በቤተ መንግሥት አሉላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ያማረ ልብስ የለበሰውን ሰውን? እነሆ፥ ጌጠኛ ልብስ የሚለብሱና በቅምጥልነት የሚኖሩ በነገሥታት ቤት አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱና በድሎት የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቀጭን ልብስ የለበሰውን ሰውን? እነሆ፥ ጌጠኛ ልብስ የሚለብሱና በቅምጥልነት የሚኖሩ በነገሥታት ቤት አሉ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 7:25
16 Referencias Cruzadas  

ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?


የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም የማ​ዕ​ዱን መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።


እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።


ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ።


አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።


“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።


የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን?


ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ነቢ​ይን ነውን? አዎን፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከነ​ቢ​ይም ይበ​ል​ጣል።