ሉቃስ 17:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነመ፤ ሁሉንም አጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ዕለት ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ በሙሉ አጠፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ፤ ሁሉንም አጠፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ። |
የመንግሥታት ክብር፥ የከለዳውያንም የትዕቢታቸው ትምክሕት የሆነች ባቢሎንም እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።
ሰዶምንና ገሞራን፥ በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም፤ የሰውም ልጅ አይኖርባትም።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።
ሰዶምንና ገሞራን አስቀድሜ እንደ ገለበጥኋቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፤ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ በዚህም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።