የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና።
ዘሌዋውያን 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ኀጢአት ነው፤ በመካከላቸው ኀጢአት እንዳይሆን እርሱንና እነርሱን በእሳት ያቃጥሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቷን ቢያገባ፣ አድራጎቱ ጸያፍ ነው፤ በመካከላችሁ እንዲህ ዐይነት ርኩሰት እንዳይገኝ ሰውየውና ሴቶቹ በእሳት ይቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ዝሙት ነው፤ በመካከላችሁ አመንዝራ እንዳይኖር እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው እናትና ሴት ልጅዋን ቢያገባ፥ ስለ ፈጸሙት ክፉ ድርጊት ሦስቱም በእሳት ተቃጥለው ይገደሉ፤ እንዲህ ያለው ነገር በመካከላችሁ መፈጸም የለበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ። |
የሴትንና የሴት ልጅዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ኀጢአት ነውና።
የድሆችን ራስ ይቀጠቅጣሉ፤ የትሑታንንም ፍርድ ያጣምማሉ፤ የአምላካቸውንም ስም ያረክሱ ዘንድ አባትና ልጁ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤
“ከአማቱ ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። ከዋርሳው ጋር የሚተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይሁን ይላሉ።
ምልክት የታየበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና፥ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።”
ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው።