ዘሌዋውያን 16:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፤ የሀገር ልጅም፥ በእናንተም መካከል የተቀመጠ እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትነጹበት ስርየት በዚህች ዕለት ይደረግላችኋልና፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኀጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተ በዚህ ቀን እንድትነጹ ማስተስረያ ይደረግላችኋልና፤ በጌታም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዕለት ንጹሖች እንድትሆኑ የኃጢአት ማስተስረይ ይደረግላችኋል፤ ከዚያም ከኃጢአታችሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የነጻችሁ ትሆናላችሁ፤ |
እኔንም ከበደሉበት ኀጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ እኔም የበደሉኝንና ያመፁብኝን ኀጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።
“በዚህ በሰባተኛው ወር ዐሥረኛዋ ቀን የማስተስረያ ቀን ናት፤ ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ።
በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ ማስተስረያ ትሆንላችሁ ዘንድ የማስተስረያ ቀን ናትና በዚያች ቀን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።