ዘሌዋውያን 13:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ካህኑ ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተደረገ ነገር ቢሆን በልብሱ ላይ ባይሰፋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ ደዌው በልብሱ ወይም በሸማኔ ዕቃ በተሠራው ወይም በእጅ በተጠለፈው ጨርቅ ላይ፣ ወይም ከቈዳ በተሠራው ዕቃ ላይ ተስፋፍቶ ካልተገኘ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካህኑ ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ ባይሰፋ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ ሻጋታው ተስፋፍቶ ካልተገኘ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑ ቢያይ፥ እነሆም፥ ደዌው በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ቢሆን በልብሱ ላይ ባይሰፋ፥ |
ልብሱን ያቃጥላል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጕር ወይም የተልባ እግር ቢሆን ወይም ከቆዳ የተደረገ ቢሆን፥ ደዌ ያለበት ሁሉ እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነውና በእሳት ይቃጠላል።