መሳፍንት 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይኑም፦ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጅነቴን ትቼ በዛፎች ላይ እነግሥ ዘንድ ልሂድን? አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የወይን ተክሉም፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ አማልክትንና ሰዎችን ደስ የሚያሠኘውን የወይን ጠጄን መስጠት ልተውን?’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይን ተክሉም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ አማልክትንና ሰዎችን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን መስጠት ልተውን?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ተክሉ ግን ‘አማልክትንና ሰዎችን የሚያስደስተውን የወይን ጠጄን መስጠቴን አቁሜ በዛፎች ላይ ለመንገሥ ልሂድን?’ ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይኑም፦ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው። |
የሰው ልጆች በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች የሚሠሩት መልካም ነገር ምን እንደ ሆነ እስካይ ድረስ ልቤ በጥበብ እየመራኝ፥ ሰውነቴን በወይን ደስ ለማሰኘት፥ ስንፍናንም ለመያዝ በልቤ መረመርሁ።
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ ወይን ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።