መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
መሳፍንት 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱ ላይ ወረደ፤ የእስራኤል መስፍን ሆኖ ወደ ጦርነትም ወጣ። እግዚአብሔር የአራም ንጉሥ ኵስርስቴምን አሳልፎ ስለ ሰጠው ድል አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ፥ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፥ ለሰልፍ ወጣ፥ እግዚአብሔርም የመሰጴጦምያን ንጉሥ ኩሰርሰቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እጁም በኩሰርሰቴም ላይ አሸነፈች። |
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በምታንያስ ልጅ በኢያሔል ልጅ በብልአንያ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በኡዝሔል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤
እኔም እወርዳለሁ፤ በዚያም አነጋግርሃለሁ፤ በአንተ ካለውም መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፤ አንተም ብቻ እንዳትሸከም የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።
እግዚአብሔርም በደመናው ወረደ፤ ተናገረውም፤ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ፤ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተጨመረላቸውም።
ሙሴም “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያሳድር አንተ ስለ እኔ ትቀናለህን?” አለው።
ነገር ግን አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን፥ ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን፥ ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን፥
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም።
የአህያ መንጋጋ አጥንት ወደ ተባለ ቦታም ደረሰ፤ ፍልስጥኤማውያንም ደንፍተው ተቀበሉት፤ ወደ እርሱም ሮጡ። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በክንዱም ያሉ እነዚያ ገመዶች በእሳት ላይ እንደ ተጣለ ገለባ ሆኑ፤ ማሰሪያውም ከክንዱ ተፈታ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወንዞችም መካከል ባለች በሶርያ ንጉሥ በኩሳርሳቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኩሳርሳቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።
ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአንተ ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለወጣለህ።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።