መሳፍንት 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም፥ “በሰባት ባልደረቀ በርጥብ ጠፍር ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ፤ እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ” አላት ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳምሶንም፣ “ማንም ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስረኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምሶንም፥ “ማንም ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስረኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶምሶንም “እርጥብ በሆኑ ሰባት አዳዲስ ጠፍሮች ቢያስሩኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶምሶንም፦ በሰባት ባልደረቀ በእርጥብ ጠፍር ቢያስሩኝ፥ እደክማለሁ እንደ ሌላ ሰው እሆናለሁ አላት። |
በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል።
ደሊላም ሶምሶንን፥ “እነሆ፥ አታለልኸኝ፤ የነገርኸኝም ሐሰት ነው፤ አሁንም የምትታሰርበት ምን እንደሆነ፥ እባክህ ንገረኝ” አለችው።
የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተደብቀው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱም ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፤ ኀይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም።
ሳኦልም ሜልኮልን አላት፥ “ስለምን እንዲህ አታለልሽኝ? ጠላቴን አስኰበለልሽ፤ እንዲያመልጥም አደረግሽው?” ሜልኮልም ለሳኦል፥ “እርሱ፦ አውጥተሽ ስደጂኝ፤ አለዚያ እገድልሻለሁ አለኝ” አለችው።
አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው።