የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
መሳፍንት 1:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞናውያንም ድንበር ከአቅራቢም ዐቀበት ከጭንጫው ጀምሮ እስከ ላይኛው ድረስ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞራውያን ድንበር አቅራቢያም መተላለፊያ እስከ ሴላዕና ከዚያም የሚያልፍ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሞራውያን ድንበር አቅራቢያም መተላለፊያ እስከ ሴላዕና ከዚያም የሚያልፍ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሞራውያን ድንበር ከዐቅራቢም አቀበት ከሴላዕ ጀምሮ ወደ ላይ ይወጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞራውያንም ድንበር ከአቅረቢም ዐቀበት ከጭንጫው ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ ነበረ። |
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
ዳርቻችሁም በአቅራቦን ዐቀበት በአዜብ በኩል ይዞራል፤ እስከ ኤናቅም ይደርሳል፤ መውጫውም በቃዴስ በርኔ በአዜብ በኩል ይሆናል፤ ወደ አራድ ሀገሮችም ይደርሳል፤ ወደ አሴሞናም ያልፋል፤
አሞሬዎናውያንም ድብና ቀበሮዎች በሚኖሩበት በመርስኖኖስ ተራራ መቀመጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ወገን እጅ በአሞሬዎናውያን ላይ ጸናች፤ ገባርም አደረጉአቸው።