ዮሐንስ 4:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሠራሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ የመሰከረችው ሴት ስለ ነገረቻቸውም ከዚያች ከሰማርያ ከተማ ብዙዎች አመኑበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቲቱም፣ “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ ስለ መሰከረች፣ ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በርሱ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ፤” ብላ በመሰከረችው ቃል መሠረት፥ ከዚያች ከተማ፥ ብዙ የሰማርያ ሰዎች በእርሱ አመኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋ “የሠራሁትን ነገር ሁሉ ነገረኝ” ብላ በመሰከረችው መሠረት ከዚያ ከተማ ብዙዎቹ የሰማርያ ሰዎች አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም፦ ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ ብላ ስለ መሰከረችው ቃል ከዚያች ከተማ የሰማርያ ሰዎች ብዙ አመኑበት። |
ስለዚህ ከአይሁድም ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው የነበሩ ብዙ ሰዎች ጌታችን ኢየሱስ ያደረገውን አይተው በእርሱ አመኑ።
ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።