Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 4:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 እኔም ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን እን​ድ​ታ​ጭዱ ላክ​ኋ​ችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እና​ን​ተም በድ​ካ​ማ​ቸው ገባ​ችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ አድካሚውን ሥራ ሌሎች ሠሩ፤ እናንተም የድካማቸውን ፍሬ ሰበሰባችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እናንተም እነርሱ በደከሙበት ገባችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች በሥራ ደከሙ፤ እናንተ ግን በድካማቸው ፍሬ ተጠቀማችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 4:38
20 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም ሁሉ በእ​ርሱ በኩል እን​ዲ​ያ​ምን ስለ ብር​ሃን ይመ​ሰ​ክር ዘንድ ለም​ስ​ክ​ር​ነት መጣ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝ​ቡና ለማ​ደ​ሪ​ያው ስላ​ዘነ ማለዳ ተነ​ሥቶ በነ​ቢ​ያቱ እጅ ወደ እነ​ርሱ ይልክ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምእ​መ​ናን እጅግ በዙ፤ ከካ​ህ​ና​ትም መካ​ከል ያመኑ ብዙ​ዎች ነበሩ።


በጌ​ታ​ች​ንም የሚ​ያ​ምኑ ብዙ​ዎች ይጨ​መሩ ነበር፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።


ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ።


ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም።


ቃሉ​ንም ተቀ​ብ​ለው ተጠ​መቁ፤ በዚ​ችም ዕለት ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተጨ​መሩ።


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


አንዱ ይዘ​ራል፥ ሌላ​ውም ያጭ​ዳል የሚ​ለው ቃል በዚህ እው​ነት ሆኖ​አል።


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ ነገ​ረኝ” ብላ የመ​ሰ​ከ​ረ​ችው ሴት ስለ ነገ​ረ​ቻ​ቸ​ውም ከዚ​ያች ከሰ​ማ​ርያ ከተማ ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በት።


አንተ እኔን ወደ ዓለም እንደ ላክ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን ወደ ዓለም ላክ​ኋ​ቸው።


እኛስ በማ​ይ​ገባ ሌላ በደ​ከ​መ​በት አን​መ​ካም፤ ነገር ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ሰፋ፥ የተ​ሠ​ራ​ች​ላ​ችሁ ሕግም በእ​ና​ንተ እን​ድ​ት​ጸና ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios