ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
ዮሐንስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ቀን የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌታችን የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛው ቀን፣ በገሊላ አውራጃ፣ በቃና ከተማ ሰርግ ነበር፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን፥ በገሊላ ምድር በምትገኘው ቃና በምትባል ከተማ ሠርግ ነበረ፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ |
ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
እርሱም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ወሰደው፤ ጌታችን ኢየሱስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባላለህ፤” አለው፤ ትርጓሜውም ጴጥሮስ ማለት ነው።
ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።
ስምዖን ጴጥሮስ፥ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ፥ ከገሊላ ቃና የሆነው ናትናኤል፥ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎችም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት አብረው ነበሩ።
ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።