La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 19:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጭፍ​ሮ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በሰ​ቀ​ሉት ጊዜ ልብ​ሶ​ቹን ወስ​ደው ከጭ​ፍ​ሮቹ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት ክፍል አድ​ር​ገው መደ​ቡት፤ ቀሚ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ቀሚ​ሱም ከላይ ጀምሮ የተ​ሠራ ሥረ​ወጥ እንጂ የተ​ሰፋ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉ በኋላ፣ እጀ ጠባቡ ሲቀር፣ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዱ አንድ አንድ እንዲዳረስ ለአራት ተከፋፈሉት፤ እጀ ጠባቡም ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለ ስፌት የተሠራ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወታደሮቹም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ በአራት ከፋፈሉአቸው፤ እጀ ጠባቡንም እንዲሁ ወሰዱ። እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ፥ ልብሶቹን ወስደው፥ ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ በአራት ከፋፈሉአቸው፤ እጀ ጠባቡንም እንዲሁ አደረጉ፤ ነገር ግን እጀ ጠባቡ ሳይሰፋ፥ ከላይ እስከ ታች ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 19:23
6 Referencias Cruzadas  

ከላ​ይም በመ​ካ​ከል አን​ገ​ትጌ ይሁ​ን​በት፤ እን​ዳ​ይ​ቀ​ደ​ድም በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ ጥልፍ በአ​ን​ገ​ት​ጌው ዙሪያ ይሁ​ን​በት።


ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፤


ሰቀሉትም፤ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ኣያ​ው​ቁ​ምና ይቅር በላ​ቸው” አለ፤ በል​ብ​ሱም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣ​ሉና ተካ​ፈሉ።


ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።