ሳኦልና ዮናታን የተወደዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
ኢዮብ 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመርከብ መንገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚበርና የሚበላውን የሚፈልግ የንስር ፍለጋ እንደማይታወቅ ሕይወቴ እንዲሁ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበርር ንስር ይፈጥናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ ይሮጣሉ፤ እንደ ነጣቂ ንስርም ይፈጥናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል። |
ሳኦልና ዮናታን የተወደዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል። ፈጣኖች መልእክተኞች ወደ ረዥምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቈረጡና የተረገጡ ሕዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሀገር ይኖራሉ።
እነሆ! እንደ ደመና ይወጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ተዋርደናልና ወዮልን።
ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።