እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
ኢዮብ 42:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፤ መንጋዎቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። እርሱም ዐሥራ አራት ሺሕ በጎች፣ ስድስት ሺሕ ግመሎች፣ አንድ ሺሕ ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺሕ እንስት አህዮችም ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፥ ዐሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለኢዮብ ባረከ፥ አሥራ አራት ሺህም በጎች፥ ስድስት ሺህም ግመሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም እንስት አህዮች ነበሩት። |
እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፤ አገነነውም፤ ላሞችንና በጎችን፥ ወርቅንና ብርን፥ ወንዶች ባሪያዎችንና ሴቶች ባሪያዎችን፥ ግመሎችንና አህዮችንም ሰጠው።
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።
ሰውንና እንስሳውንም አበዛላችኋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ያፈሩማል፤ እንደ ጥንታችሁም ሰዎችን አኖርባችኋለሁ፤ ቀድሞም እንደ አደረግሁላችሁ መልካም አደርግላችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግልህ ዘንድ ሊፈትንህ፥ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ የመገበህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ፥
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።