ኢዮብ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመከራ ሳለህ ነገር አታብዛ፥ የነገር ብዛት ምን ይጠቅምሃል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ከአንተ ጋራ ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን? ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን? ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኢዮብ ሆይ! አንድ ሰው ደፍሮ ቢናገርህ በትዕግሥት ታዳምጣለህን? ነገር ግን ከመናገር ማን ይቈጠባል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ከአንተ ጋር ይናገር ዘንድ ቢሞክር ትቀይማለህን? ቃልንስ ከመናገር ሊቀር የሚችል ማን ነው? |
እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስሙ አልናገርም፥” በአጥንቶች ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፤ መሸከምም አልቻልሁም።
ስለዚህ ቍጣዬን መላሁባቸው፤ ታገሥሁ፤ ፈጽሜም አላጠፋኋቸውም፤ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጐልማሶችም ጉባኤ ላይ መዓቴን በአንድነት አፈስስባቸዋለሁ፤ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።