ለኀይለኛው ዝናብ መውረጃውን፥ ወይስ ለሚያንጐዳጕደው መብረቅ መንገድን ያዘጋጀ ማንነው?
ለዝናብ መውረጃን፣ ለመብረቅም መንገድን ያበጀ ማን ነው?
ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥
“ለዝናብ መውረጃን ያዘጋጀለት፥ ነጐድጓድ ለተቀላቀለበት ውሽንፍርም መንገድ ያበጀለት ማነው?
እነዚህን በፈጠረ ጊዜ እንዲሁ ዐውቆ ቈጠራቸው። ለዝናም ሥርዐትን ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ።
አመዳይ ከየት ይወጣል? ከሰማይ በታች ያለ የአዜብ ነፋስስ እንዴት ይበተናል?
ማንም በሌለበት ምድር ላይ፥ ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ ይዘንም ዘንድ፥
ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤