ኢዮብ 38:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አመዳይ ከየት ይወጣል? ከሰማይ በታች ያለ የአዜብ ነፋስስ እንዴት ይበተናል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መብረቅ ወደሚሠራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣ የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፋፈላል? የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርሃን የሚከፋፈልበት ቦታ ወዴት ነው? ወይስ ደረቅ ነፋስ በምድር ላይ የሚሠራጭበት ቦታ ወዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፈላል? የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል? |
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስን አዘዘ፤ ዮናስንም እስኪዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕይወት ሞት ይሻለኛል” አለ።