ኢዮብ 37:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሰወረ ማደሪያውም ችግር፥ ከተራሮች ጫፍም ብርድ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ነፋስ ከደቡብ ይነሣል። ብርዳማ ነፋስም ከሰሜን ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል። |
ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ የአጥቢያ ከዋክብትንም፥ በአዜብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ፈጥሮአል።
ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ ሀገር ከምድረ በዳ ይመጣል።
እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።