ኢዮብ 32:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ፊት ማድላትን አላውቅም፤ ከሰውም የተነሣ የማፍረው ካለ ትሎች ይብሉኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማቈላመጥን ባውቅበትማ ኖሮ፣ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ባጠፋኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማቈላመጥ መናገር አላውቅምና፥ ያለዚያስ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ባጠፋኝ ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ሰውን ማቈላመጥ አይሆንልኝም፤ ይህንንም ባደርግ ፈጣሪዬ በፍጥነት ይቀጣኝ ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማቈላመጥ እናገር ዘንድ አላውቅምና፥ ያለዚያስ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ከሕይወቴ ይለየኝ ነበር። |
አሁንስ ለእግዚአብሔር ያይደለ ለሰው ብዬ አስተምራለሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰኛለሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም።