ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
ኢዮብ 30:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፣ ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጋራ እንዳይቀመጡ፣ አባቶቻቸውን የናቅኋቸው፣ እነዚህ ይሣለቁብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሰዎች ያፌዙብኛል፤ የእነርሱ አባቶች የበጎቼን መንጋ ከሚጠብቁ ውሾቼ ጋር እንኳ እንዲሰማሩ የምንቃቸው ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ውሾች ጋር ለማኖር የናቅኋቸው፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ። |
ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።
እንዲህም አላቸው፥ “ይህን ሰው ሕዝብን ያሳምፃል ብላችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፤ በፊታችሁም እነሆ፥ መረመርሁት፤ ግን እናንተ ካቀረባችሁት ክስ በዚህ ሰው ላይ ያገኘሁት አንዳች በደል የለም።
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር፤ አለቆችም፥ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር።
አብረው ተሰቅለው ከነበሩት አንዱ ወንበዴ፥ “አንተስ ክርስቶስ ከሆንህ ራስህን አድን፤ እኛንም አድነን” ብሎ ተሳደበ።
የማያምኑ አይሁድ ግን ቀኑባቸው፤ ከገበያም ክፉዎች ሰዎችን አምጥተው፥ ሰዎችንም ሰብስበው ሀገሪቱን አወኳት፤ ፈለጓቸውም፤ የኢያሶንን ቤትም በረበሩ፤ ወደ ሕዝቡም ሊያወጧቸው ሽተው ነበር።